Quantcast
Channel: Articles
Viewing all articles
Browse latest Browse all 139

ደምዳሚ (ድምዳሜ) ማስረጃ ምንድነው?

$
0
0
  1. የተሟላና ሙሉ ዕምነት የሚጣልበት ማስረጃ

የልዩ አዋቂ /expert/ የሚደርስበት የመጨረሻ አስተያየት ከሚኖረው ሙያዊ ዕውቀት አድማስ፣ ከሚታገዝበት መሣሪያና ከመሳሰሉት ጋር የተሟላና ሙሉ ዕምነት የሚጣልበት ማስረጃ /conclusive evidence/ ሊሆን ስለማይችል በዓይን ምስክሮች የተነገረን ፍሬ ነገር ለማስተባበል የሚያበቃ አቅም አይኖረውም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 43453 ቅጽ 12[1]

የትራፊክ ፖሊስ የአደጋ ፕላን ሪፖርት የባለሙያ ሙያዊ አስተያየትን በወረቀት ላይ ስዕላዊ በሆነ መንገድ የሚያስቀምጥ በባለሙያ የሚረጋገጥ ሰነድ በመሆኑ እንደ ማንኛውም የልዩ አዋቂ የምስክርነት ቃል በተገቢው መንገድ ሊመዘን የሚገባው የማስረጃ አይነት እንጅ ሁልጊዜ ድምዳሜ ማስረጃ (Conclusive Evidence) ያለመሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

ሰ/መ/ቁ. 92141 ቅጽ 17[2]

  1. አሳሪ ማስረጃ

በአስተዳደር አካል የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ነው ተብሎ የምስክር ወረቀት መስጠት ማስረጃውን ደምዳሚ ወይም አሳሪ (Conclusive Evidence) የሚያደርገው አይደለም፡፡ ይልቁንም ይኸው ማስረጃ የተሰጠበት አግባብ በፍ/ህ/ህ/ቁ. 1195 ድንጋጌ ስር በተመለከቱት ሁኔታዎች መሰረት ስለመሆኑ ማስረዳት ከተቻለ በፍ/ህ/ቁ. 1195 ስር የተመለከተው ሕጋዊ ግምት ሊስተባበል የሚችል (rebuttable legal presumption) መሆኑን ከድንጋጌዎቹ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡

ሰ/መ/ቁ. 64014 ቅጽ 13[3]

  1. ማስተባበያ ሊቀርብበት የማይችል ወሳኝ ማስረጃ

አንድ ለማይንቀሳቀስ ንብረት የተሰጠ የባለሃብትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባለሃብትነትን በተመለከተ የህግ ግምት የሚያሰጥ ቢሆንም በሌላ ተቃራኒ ማስረጃ ሊስተባበል፣ በተቃራኒው ከሚቀርቡት ማስረጃዎች ጋር ሊመዘን የሚችል እንጂ እንጅ ማስተባበያ ሊቀርብበት የማይችል ወሳኝ /conclusive evidence/ ያለመሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡

ሰ/መ/ቁ. 67011 ቅጽ 13[4]

  1. የመጨረሻ ማስረጃ

የልጅነት ሁኔታ መኖሩን ማስረዳት ከተቻለ ፍ/ቤት ልጅ ነው ሲል የሕግ ግምት ሊወስድ የሚችል መሆኑን የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 157/1/ ያመለክታል፡፡ ከአንቀፁ መረዳት እንደሚቻለው የልጅነት ሁኔታ መኖሩን ማረጋገጥ የመጨረሻ ማስረጃ (conclusive evidence) ሳይሆን የሕግ ግምት ብቻ ነው፡፡ ግምቱም ቢሆን አስገዳጅነት ያለው የሕግ ግምት አይደለም፡፡ ግምቱን የሚቃወም ወገን ማስረጃ በማቅረብ ማፍረስ እንደሚችል ንዑስ አንቀፅ 2 ይደነግጋል፡፡

ሰ/መ/ቁ. 42648 ቅጽ 10[5]

  1. ክርክር ሊነሳበት የማይችል ማስረጃ

ልጅነት የሚረጋገጥበት ዋናው ማስረጃ የልደት ምስክር ወረቀት እንደሆነ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 154 ላይ ተመልክቷል፡፡ ይህ ማለት ግን የልደት ምስክር ወረቀት ክርክር ሊነሳበት የማይችል ሙሉ እምነት ሊጣልበት የሚችል /Conclusive/ ማስረጃ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 33440 ቅጽ 5[6]

[1] አመልካች አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት እና ተጠሪዎች እነ ወ/ሮ ዘነበወርቅ ከበደ ህዳር 15 ቀን 2002 ዓ.ም.

[2] አመልካች የደ/ብ/ብ/ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትሕ ቢሮ እና ተጠሪአቶ አለማየሁ አስፋው መስከረም 30 ቀን 2007 ዓ.ም.

[3] አመልካች ዶ/ር ገነት ስዩም እና ተጠሪ እነ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 17/18 አስተዳደር ጽ/ቤት /3 ሰዎች/   የካቲት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

[4] አመልካቾች እነ የወ/ሮ ጣይቱ ከበደ ወራሾች /2 ሰዎች/ እና ተጠሪ እነ ወ/ሮ ጥሩነሽ ኃይሌ /3 ሰዎች/ መጋቢት 11 ቀን 2004 ዓ.ም.

[5] አመልካች ወ/ሮ ዘነበች በያን እና ተጠሪ ወ/ት ብርቅነሽ ከበደ ታህሳስ 6 ቀን 2002 ዓ.ም.

[6] አመልካች ወ/ሮ ኪሮስ ገ/ማርያም እና ተጠሪ አቶ ግርማ ገብረስላሴ ሚያዝያ 21 ቀን 2000 ዓ.ም.


Filed under: Articles, Case Comment

Viewing all articles
Browse latest Browse all 139

Trending Articles